Thursday, 20 June 2019

የኢፌዴሪት ትራንስፖርትባለስልጣን

በኢትዮጵያ 1 ተሽከርካሪ በአማካኝ ለ100 ሰው ይደርሳል፡- የኢፌዴሪት ትራንስፖርትባለስልጣን
******************************
በኢትዮጵያ ያለው የተሽከርካሪ ብዛት ከአለም አገራት እና ካለው የህዝብ
ብዛት አንፃር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በአገሪቱ ያለው የተሽከርካሪ ቁጥር ከሰው ስብጥር አንጻር 1 ተሽከርካሪ
በአማካኝ ከ100 በላይ ለሚሆን ህዝብ እያገለገለ መሆኑን ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ በታሪክ ከአፍሪካ አገራት ቀደም ብላ መኪና ለማስገባትና
ለመጠቀም ብትችልም በአሁኑ ሰአት ግን ያለው የመኪና ብዛት ከጎረቤት
አገራት ጋር እንኳን ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑ ይነገራል፡፡
ከኢፌዴሪ ትራንስፖርት ባለስልጣን በተገኘው መረጃ መሰረት እስከ
ታህሳስ 30/2011 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ያለው የመኪና ብዛት 977
ሺህ 349 ነው፡፡
ይህም ሆኖ ግን የህብረተሰቡ የመኪና ፍላጎት እና የመግዛት አቅም
እያደገ መምጣቱን ተከትሎ በአገራችን ያለው የተሽከርካሪ ቁጥር
በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን
ይገልፃል፡፡
የተሽከርካሪ ቁጥር እያደገ ቢመጣም ግን ከሌሎች የአለም አገራትና
ካለው የህዝብ ብዛት ጋር ሲነጻጸር ያለው የመኪና ቁጥር እጅግ ዝቅተኛ
መሆኑን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው
ገልፀዋል፡፡
ካለው 1 ሚሊዮን ገደማ ተሽከርካሪ ውስጥ 62 በመቶ የሚሆነው
በመዲናችን አዲስ አበባና በዙሪያዋ እንደሚገኝም ከባለስልጣን መስሪያ
ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ካደጉት አገራት ተርታ የምትመበዋ ስዊድን 9 ሚሊዮን ህዝብ ይዛ ከ5
ሚሊዮን በላይ ተሽከርካሪ ሲኖራት ጎሮቤት አገር ኬኒያ ደግሞ ከ50
ሚሊዮን ለማይበልጡት ዜጎቿ 3 ሚሊዮን የሚጠጋ ተሽከርካሪዎች አላት፡፡
ኬኒያ ከኢትዮጵያ በግማሽ የሚያንስ የህዝብ ብዛት ቢኖራትም
በተሽከርካሪ ብዛት ከኢትዮጵያ በ3 እጥፍ ትበልጣለች፡፡
የትራንስፖርት ባለስልጣን የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማርካት ከዉጭ
ተሽከርካሪዎችን የሚያስገቡና በአገር ውስጥ አዳዲስ ተሽከርካሪዎችን
የሚያመርቱ ተቋማት ቁጥር እንዲጨምር በተጠናከረ ሁኔታ እየሰራ
መሆኑንም አስታውቋል፡፡

No comments: