Ethiopian news
Friday, 21 June 2019
የ2011 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብሔራዊ ፈተናተ ተጠናቀቀ
የ2011 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብሔራዊ ፈተናተ ተጠናቀቀ
********************
በመላው ሀገሪቱ ከሰኔ 6-11/2011 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል
የ2011 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብሔራዊ ፈተና
በሰላም መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
ሀገር አቀፍ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቃቅ መምህራን፤ ተማሪዎች፣
የትምህርት አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ወላጆች፣ የፀጥታ አካላትና ሌሎች
ባለድርሻ አካላትን እንዲሁም መላ የሀገራችን ህዝቦች ጎላ ሚና
እንደነበራቸዉም ነው የተገለፀው፡፡
ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች በእረፍት ጊዜያቻ ታናሾቻችሁን
በማስጠናት፣ወላጆቻችሁን በመርዳትና የክረምት በጎፍቃድ አገልግሎት
ላይ በመሰማራት አርዓያ እንድሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅቧል፡፡
Thursday, 20 June 2019
የኢፌዴሪት ትራንስፖርትባለስልጣን
በኢትዮጵያ 1 ተሽከርካሪ በአማካኝ ለ100 ሰው ይደርሳል፡- የኢፌዴሪት ትራንስፖርትባለስልጣን
******************************
በኢትዮጵያ ያለው የተሽከርካሪ ብዛት ከአለም አገራት እና ካለው የህዝብ
ብዛት አንፃር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በአገሪቱ ያለው የተሽከርካሪ ቁጥር ከሰው ስብጥር አንጻር 1 ተሽከርካሪ
በአማካኝ ከ100 በላይ ለሚሆን ህዝብ እያገለገለ መሆኑን ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ በታሪክ ከአፍሪካ አገራት ቀደም ብላ መኪና ለማስገባትና
ለመጠቀም ብትችልም በአሁኑ ሰአት ግን ያለው የመኪና ብዛት ከጎረቤት
አገራት ጋር እንኳን ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑ ይነገራል፡፡
ከኢፌዴሪ ትራንስፖርት ባለስልጣን በተገኘው መረጃ መሰረት እስከ
ታህሳስ 30/2011 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ያለው የመኪና ብዛት 977
ሺህ 349 ነው፡፡
ይህም ሆኖ ግን የህብረተሰቡ የመኪና ፍላጎት እና የመግዛት አቅም
እያደገ መምጣቱን ተከትሎ በአገራችን ያለው የተሽከርካሪ ቁጥር
በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን
ይገልፃል፡፡
የተሽከርካሪ ቁጥር እያደገ ቢመጣም ግን ከሌሎች የአለም አገራትና
ካለው የህዝብ ብዛት ጋር ሲነጻጸር ያለው የመኪና ቁጥር እጅግ ዝቅተኛ
መሆኑን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው
ገልፀዋል፡፡
ካለው 1 ሚሊዮን ገደማ ተሽከርካሪ ውስጥ 62 በመቶ የሚሆነው
በመዲናችን አዲስ አበባና በዙሪያዋ እንደሚገኝም ከባለስልጣን መስሪያ
ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ካደጉት አገራት ተርታ የምትመበዋ ስዊድን 9 ሚሊዮን ህዝብ ይዛ ከ5
ሚሊዮን በላይ ተሽከርካሪ ሲኖራት ጎሮቤት አገር ኬኒያ ደግሞ ከ50
ሚሊዮን ለማይበልጡት ዜጎቿ 3 ሚሊዮን የሚጠጋ ተሽከርካሪዎች አላት፡፡
ኬኒያ ከኢትዮጵያ በግማሽ የሚያንስ የህዝብ ብዛት ቢኖራትም
በተሽከርካሪ ብዛት ከኢትዮጵያ በ3 እጥፍ ትበልጣለች፡፡
የትራንስፖርት ባለስልጣን የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማርካት ከዉጭ
ተሽከርካሪዎችን የሚያስገቡና በአገር ውስጥ አዳዲስ ተሽከርካሪዎችን
የሚያመርቱ ተቋማት ቁጥር እንዲጨምር በተጠናከረ ሁኔታ እየሰራ
መሆኑንም አስታውቋል፡፡

Monday, 17 June 2019
በከፍተኛ ሊግ ሲወዳደሩ የቆዩት ሰበታ ከተማ
ሰበታ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና የእግርኳስ ክለቦች ወደ
ፕሪምየር ሊጉ አደጉ
*******************
በከፍተኛ ሊግ ሲወዳደሩ የቆዩት ሰበታ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ እና
ሀዲያ ሆሳዕና የእግርኳስ ክለቦች ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በከፍተኛ ሊጉ ምድብ “ሀ” የሚገኘው ሰበታ ከተማ ከተከታዩ ለገጣፎ
ለገዳዲ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 አቻ በሆነ ውጤት በማጠናቀቅ 1
ጨዋታ እየቀረው ለ2012 ዓ.ም ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡
በምድብ “ለ” የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ ደግሞ ከሜዳው ውጪ
ከነገሌ አርሲ ጋር በተመሳሳይ 1 አቻ ተለያይቶ አንድ ጨዋታ እየቀረው
ወደ 2012 ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡
በምድብ “ሐ” ሲወዳደር የቆየው ሀዲያ ሆሳዕና በሜዳው ከምባታ
ሺንሺቾን 3-0 አሸንፎ 2 ጨዋታ እየቀረው ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን
ያረጋገጠበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡
በ2008 ዓ.ም ከፕሪምየር ሊጉ የወረደው ሀዲያ ሆሳዕና ከ3 የውድድር
ዘመን በኋላ ወደ ሊጉ የተመለሰ ሲሆን በ2003 ዓ.ም ከፕሪምየር ሊጉ
የወረደው ሰበታ ከተማ ከ8 የውድድር ዘመናት በኋላ ተመልሷል።
ወልቂጤ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ
መሆኑም ታውቋል፡፡
ሶከር ኢትዮጵያ
Subscribe to:
Posts (Atom)