ሰበታ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና የእግርኳስ ክለቦች ወደ
ፕሪምየር ሊጉ አደጉ
*******************
በከፍተኛ ሊግ ሲወዳደሩ የቆዩት ሰበታ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ እና
ሀዲያ ሆሳዕና የእግርኳስ ክለቦች ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በከፍተኛ ሊጉ ምድብ “ሀ” የሚገኘው ሰበታ ከተማ ከተከታዩ ለገጣፎ
ለገዳዲ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 አቻ በሆነ ውጤት በማጠናቀቅ 1
ጨዋታ እየቀረው ለ2012 ዓ.ም ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡
በምድብ “ለ” የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ ደግሞ ከሜዳው ውጪ
ከነገሌ አርሲ ጋር በተመሳሳይ 1 አቻ ተለያይቶ አንድ ጨዋታ እየቀረው
ወደ 2012 ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡
በምድብ “ሐ” ሲወዳደር የቆየው ሀዲያ ሆሳዕና በሜዳው ከምባታ
ሺንሺቾን 3-0 አሸንፎ 2 ጨዋታ እየቀረው ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን
ያረጋገጠበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡
በ2008 ዓ.ም ከፕሪምየር ሊጉ የወረደው ሀዲያ ሆሳዕና ከ3 የውድድር
ዘመን በኋላ ወደ ሊጉ የተመለሰ ሲሆን በ2003 ዓ.ም ከፕሪምየር ሊጉ
የወረደው ሰበታ ከተማ ከ8 የውድድር ዘመናት በኋላ ተመልሷል።
ወልቂጤ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ
መሆኑም ታውቋል፡፡
ሶከር ኢትዮጵያ

No comments:
Post a Comment